የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

[ተመዛኞች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በጥሞና ማንበብና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው]

**************************************

 1. አመልካቾች በዚህ የኦንላይን ሲስተም (online system) ለመመዝገብ ላፕቶፕ/ኮምፒውተር ቢጠቀሙ መልካም ነው፡፡ ሞባይል መጠቀም ይቻላል ነገር ግን አንዳንድ ረዘም ያሉ ጽሁፎች እና ምስሎች ላይታዩ ይችላሉ፡፡
 2. በዚህ የኦንላይን ሲስተም (online system) መመዝገብ የሚችሉት ከዚህ ቀደም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ወስደው ፈተናውን ያላለፉ ተመዛኞች ብቻ ናቸው ፡፡
 3. በዚህ የ online registration system ለመመዝገብ ተመዛኞች የ ኢሜይል(email) አድራሻ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 4. በ online system ለመመዝገብ ተመዛኞች ጉርድ ፎቶ እና መታወቂያ ወይም passport ስካን አድርገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች የስም ዝርዝራቸው ከተማሩበት ተቋም በቀጥታ ስለሚላክልን በዚህ ኦን- ላይን ምዝገባ (online registration) መመዝገብ የለባቸውም ፡፡
 6. ዳግም ምዘና (Re-exam) የሚወስዱ ተመዛኞች የብቃት ምዘና ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉበትን ከተማ ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ መምረጥ ይኖርባቸዋል ፡፡
 7. ዳግም ምዘና (Re-exam) የሚወስዱ ተመዛኞች ለፈተናው የተመደቡበትን የፈተና ጣቢያ (assessment center) ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ በድረ-ገጽ www.moh.gov.et ወይም በfacebook: Ministry of health, Ethiopia በመግባት መመልከት ይችላሉ፡፡
 8. ተመዛኞች የonline ምዝገባቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጣቸውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration ID) መዝግበው /ፕሪንት አድርገው መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ተመዛኞች በምዘና ወቅት እርሳስ፣ መቅረጫ፣ ላጲስ እና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ከነዚህ ውጪ የእጅ ሰዓት፣ ሞባይል ስልክ የመሳሰሉትን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ፈተና ክፍል ይዘው መግባት አይችሉም፡፡
 10. የፈተና ፕሮግራሙን ከተማራችሁበት የትምህርት ተቋም እና ከላይ ከተጠቀሱት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ማግኘት ይቻላል፡፡
 11.  የ online ምዝገባቸውን ጀምረው ሳይጨርሱ ያቋረጡ አመልካቾች ዋናው ገጽ ላይ System login የሚለውን ሊንክ በመጫን email እና password አስገብተው ምዝገባቸውን ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡  

**************************************

መተግበሪያውን መጠቀሙን በመቀጠል ከላይ የተጠቀሱትን መመሪያዎች እንዳነበቡ ያረጋግጣሉ እና የሚመለከታቸውን ውሎች እና ሁኔታዎች ይቀበላሉ ፡፡
I agree and continue